በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ሶስት ማህበራት እውቅና አግኝተው ወደ ስራ ገቡ።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያግዛሉ ተብለው የተቋቋሙ ሶስት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ማህበራት እውቅና አግኝተው ወደ ስራ ገብተዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እገዛ የተቋቋሙት ማህበራቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማህበር፣ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ሰጪዎች ማህበር እና የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ናቸው። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ማህበራቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ጠንካራ ማህበር ኖሯቸው የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መደገፍ አለባቸው ብለዋል።የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ሊሳካ የሚችለው የግሉ ዘርፍ በመሪነት ሲሳተፍ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለስኬቱም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚውን ለመምራት የሚያስችል አቅም ሊፈጥርና ሊቀናጅ እንደሚገባ ተናግረዋል።ማህበራቱ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ምንጭ፡  Digital Ethiopia – ዲጂታል ኢትዮጵያ   https://www.facebook.com/digitalEthiopiaOfficial

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top